የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች

መልሱን ከታች ማግኘት ካልቻሉ፣ እባክዎን የእውቂያ ቅጹን ይጠቀሙ ወይም በኢሜል ወደ info@example.com ይላኩልን. Proflisence@gmail.com

የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ከተቋቋሙ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የተናጠል ተግባርና ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

  1. የምግቦችን ደህንነትና ጥራት፣ የመድኃኒቶችን ደህንነት፣ የፈዋሽነት፣ ጥራትና አግባባዊ አጠቃቀም፣ የህክምና ባለሙያዎችን ብቃትና አሰራር፣ የኃይጅን፣ የአካባቢ ጤናን እና የጤና-ነክ ቁጥጥር የሚደረግበት ተቋማት የቁጥጥር ደረጃዎች ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
  2. ለጤና ተቋማት፤የመድኃኒት አከፋፋዮችና ማከማቻዎች፡የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ያግድል፤ ይሰርዛል፤
  3. የጤና-ነክ ተቋማት የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፤የንጽህናና የጤና ደረጃዎችን ማሟላታቸውን ይከታታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  4. የህጻናት ማቆያዎችን የሙያ ደረጃ ፈቃድ ይሰጣል፣ የንጽህና የጤንነትና ተስማሚነት ደረጃዎችን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  5. የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ፣ የጤና ባለሙያዎች እና የጤናና ጤና-ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ተቋማትን በሚመለከት የመረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፤
  6. በምግብ ወይም በመድኃኒት መመረዝ ወይም መበከል ምክንያት ለሚደረስ ሞት፣ የጤንነት መታወክ መንስኤ የሆነውን ንጥረ ነገር ልዩ ሌዩ ናሙናዎች በመውሰድ ምንነታቸው እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤ እርምጃ ይወስዳል፤
  7. አግባብ ባለው ህግ መሰረት የባህል መድሀኒት አዋቂዎች በባህል ህክምና ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ፈቃድ ይሰጣል፤የባህል መድሀኒቱ ምን አይነት ይዘት እንዲለው በላብራቶሪ እንዲመረመር ያደርጋል፤ ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤
  8. በደረጃው የተፈቀደለት የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ያግዳል ይሰርዛል፤የባህል ህክምና ከዘመናዊ ህክምና ጎን ተጠናክሮ የሚሄድበት ስልት ይቀይሳል
  9. .በባለስልጣኑ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ተቋማት ላይ የአገልግልት ጊዜያቸው ያበቃ ምግቦች፣ መድኃኒቶችና ጥሬ እቃዎች በአግባቡ መወገዳቸውን ያረጋግጣል፤
  10. ሕገ-ወጥ ምግቦችን፣ መድኃኒቶችና የጤና አገልግልቶችን ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊ እርምጃዎችንም ይወስዳል፤
  11. አስተዳደሩ በሚቆጣጠራቸው የጤና ተቋማት አበረታች መድሀኒቶች፣ የናርኮቲክ መድኃኒት፣ ሳይኮትሮፒክ ንጥረ ነገሮች እና ፕሪከርሰር ኬሚካሎች ለህሙማን ማዘዝን፣ ማደልን፣ አጠቃቀምን፣ መመዝገብንና ሪፖርት ማድረግን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊ ሲሆን ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤
  12. በከተማው አስተዳደር ሥር ያለ ጤና-ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ተቋማት ተገቢውን የሐይጅንና አካባቢ ጤና አገልግልት መስፈርት ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
  13. የስነ-ምግባር ግድፈት በሚያሳዩ የጤና ባለሙያዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፤
  14. ለስራው አስፈላጊ የሆኑትን የጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ ያደራጃል፤ ለሚሰጠው አገልግልት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ያስከፈላል፡፡
  15. የጤና ሞያ ስነምግባር ጥሰት እና የህክምና ስህተት በመፈጸሙ አቤቶታ ወይም ጥቆማ ሲቀርብ ይመረምራል፡እንዳግባብነቱ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል
  16. የጤና ሞያ ስነምግባር ኮሚቴ አሰራር እና አደረጃጀት ደምብ አዘጋጅቶ ለከንቲባ ያቀርባል፣ሲጸድቅ ስራ ላይ ያውላል፡፡

 

  1. መረጃ የያዘውን የማመልከቻ ቅጽ ይሙሉ
  2. የአመልካቹን/የባለቤቱን (ስም፣ ዜጋ፣ አድራሻ) እና የባለቤትነት ማረጋገጫዎችን (አመልካች ስልጣን ያለው ተወካይ ከሆነ፣ የጽሁፍ የውክልና ደብዳቤ መቅረብ አለበት)፣
  3. ለነባር የጤና ተቋማት የባለቤትነት ስም እና የፍቃድ ቁጥር;
  4. የጤና ተቋሙ ስም እና ቦታ;
  5.  የጤና ተቋሙ አከባቢ;
  6.  መሰጠት ያለባቸው የአገልግሎት ዓይነቶች;
  7.  የፈቃድ ሰጭ ስም፣ ብቃት፣ ዜግነት እና የፈቃድ ቅጂ;
  8.  የሰራተኛነት (ቁጥር፣ አይነት፣ ብቃት፣ የስራ ልምድ እና የሁሉም የጤና ባለሙያዎች ኦሪጅናል የተለቀቀ እና የፈቃድ ቅጂ);
  9. የአስተዳደር ሠራተኞች ቁጥር እና ዓይነት;
  10. የባለቤትነት አይነት፡ (መንግሥታዊ፣ ሌላ መንግሥታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆነ፣ የግል ለትርፍ፣ የግል ለትርፍ ላልሆነ);
  11. የአካላዊ ፋሲሊቲ ዲዛይን እና መግለጫው;
  12.  ስራ ፈት ቦታን ለመጠቀም የታቀደ; (ካለ)
  13. የሕንፃው ባለቤት; (ኪራይ ከሆነ, የስምምነት ወረቀቱ መቅረብ አለበት);
  14.  እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርብ በመመካከር በክልሉና በሀገሪቱ ህግና ስርዓት መሰረት መሟላት ያለባቸው ሌሎች መስፈርቶች
  15.  የተደነገገውን የፍቃድ ክፍያ ይክፈሉ።
  16.  በማመልከቻ ቅጹ ላይ የተገለጸውን ማንኛውንም መረጃ ወይም ሰነድ ያቅርቡ
  17.  የጤና ተቋማቱን የመጀመሪያ ፍቃድ ለማግኘት ማመልከቻው ከዘጠና (90) ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለሚመለከተው አካል መቅረብ አለበት። የፍቃዱ ክፍያ ከማመልከቻው ጋር አብሮ ይመጣል።
  18.  የመጀመሪያው የቅድመ ፍቃድ ፍተሻ የሚመለከተው አካል በማመልከቻው ያለአገልግሎት ክፍያ ነው። በመጀመሪያ የፍቃድ አሰጣጥ ፍተሻ ወቅት ይህንን መመዘኛ ማሟላት ካልተቻለ አመልካቹ የአገልግሎት ክፍያ ሲከፍል ከሁለት ጊዜ በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ እንደገና የማመልከት መብት አለው። አመልካቹ ይህንን መስፈርት ለሶስተኛ ጊዜ ካላከበረ፣ የፈቃድ ጥያቄው ለሦስት ወራት ይታገዳል።

ጥያቄህን ጠይቅ

መልሱን ከታች ማግኘት ካልቻሉ እባክዎን መልእክት ይላኩልን.